የዩቲዩብ ቻናል አከፋፈት በጣም በሚባል ደረጃ ቀላል እንዲሁም ደግሞ ነጻ ነዉ። በተጨማሪም በአለማችን ከ ሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች በወር ዉስጥ ብቻ ዩትዩብን ይጠቀማሉ። እንዲሁም ደግሞ በየደቂቃዉ ከ 500 ሰአት በላይ የሚፈጁ ቪድዮዎች ወደዩቲዩብ ይለቀቃሉ።
የዩቲዩብ ቻናልን በሁለት አይነት መንገድ መክፈት እንችላለን።
1,የግል(personal)
ለራሳችን የምንከፍተዉ የቻናል አይነት ነዉ። ማለትም አንድ ሰዉ በራሱ ቪድዮ ሰርቶ የሚለቅበት እራሱ ቻናሉን መቆጣጠር የሚችልበት የቻናል አከፋፈት አይነት ነዉ።
ለምሳሌ:- የሀሩን ቲዩብ ቻናል
-የአሽሩካ ቻናል
-የ አቤል ብርኑ ቻናል... የመሳሰሉ ቻናሎች የግል(personal) ቻናል ናቸዉ።
2, የቢዝነስ ወይም ብራንድ ቻናል
ይህን አይነት ቻናል ደግሞ ድርጅት ካለን ማስተዋወቅ የምንፈልገዉ ብራንድ ካለን በእሱ ብቻ ትኩረት አድርገን የምንሰራበት የቻናል አይነት ሲሆን ከ ግል(personal) ቻናል ይልቅ ተጨማሪ ፊዉቸሮችን አካትቶ ይዟል።
👉በጥቅሉ በሁለቱም የቻናል አይነቶች ቪድዮ ያለገደብ መልቀቅ እንችላለን።
👉በሁለቱም የቻናል አይነቶች ገንዘብ መስራት እንችላለን።
👉ሰዎች አብዛኛውን ግዜ የ ብራንድ ቻናልን እንደ "personal" እንዲሁም ደግሞ የ"personal" ቻናልን እንደ ብራንድ ቻናል አድርገዉም ይጠቀማሉ።
በዚህ መተግበሪያ ደግሞ እንዴት አድርጋችሁ በቀላሉ ብዙም ሳትነካኩ የ"personal" ቻናል እንዴት እንደምትከፍቱ አንድ በአንድ ትመለከታላችሁ። እንዲሁም ከዚህ ገጽ መጨረሻ ላይ በዚህ ርዕስ ላይ የሚያግዙ ቪድዮዎች አሉ እነሱንም መመልከት ትችላላችሁ።
አሁን እንዴት እንደሚከፈት እንመልከት
-የዩትዩብ ቻናል ለመክፈት በመጀመሪያ የ google አካዉንት ያስፈልጋቹሀል።
-የ Google አካዉንትን መክፈት ቀላል ሲሆን እንዲሁም ነጻ ነዉ። ከዚያም ባለፈ በ Google አካዉንት በርካታ አገልግሎቶችን ማግኘት እንችላለን።
-YouTube
-Gmail
-maps
-photos እና ሌላ በርካታ አገልግሎቶችን ከጎግል አካዉን ማግኘት እንችላለን። በሌላ አገላለጽ ደግሞ ያለ ጎግል አካውንት የዩቲዩብ ቻናልን መክፈት አንችልም። የ Google አካውንት ከሌላችሁ ወይም መክፈት የምትፈልጉ ከሆነ ከዚህ ገጽ መጨረሻ አከባቢ አከፋፈቱን የሚያሳይ ቪድዮ አለላችሁ። የጎግል አካዉንት ከከፈታችሁ ቡኃላ የዩቲዩብ ቻናልን እንዴት እንደምትከፍቱ አንድ በአንድ ከታች 👇 ተከታታሉ።
1, በሞባይል
-በያዛችሁት ቀፎ የ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መኖሩን ማረጋገጥ አለባችሁ።
1. በመጀመሪያ በቀፎአቹ ወደሚገኘዉ የዩቲዩብ መተግበሪያ ትገባላችሁ።
2. ከዚያም በመቀጠል እላይ በስተቀኝ በኩል የሚገኘዉን የ ፕሮፋይል ምስል ትጫኑታላችሁ።
3. ከዚያም ከሚመጣላችሁ አማራጮች ዉስጥ "your channel" የሚለዉን አማራጭ ነካ ታደርጉታላችሁ።
4. ከዚያም በመቀጠል አሁን ከታች የመጣዉን አይነት ምስል ከመጣ "first name" እና "last name" በሚለዉ ላይ የቻናላችሁን ስም ታስገባላችሁ። ከዚያም በስተመጨረሻ የምትመለከቱትን "create channel" የሚለዉን ስትነኩት ቻናላችሁ በተሳካ ሁኔታ ይከፈታል።
"your channel" የሚለዉን ስትነኩ ከላይ ☝️ እየተመለከታችሁትን አይነት ምስል ካላመጣላችሁ እና ከታች 👇 የምትመለከቱትን አይነት ምስል ካመጣላችሁ ቻናላችሁ መጀመሪያም ተከፍቷል ማለት ነዉ።
የቻናላችሁን ስም የማትፈልጉት ከሆነ እንዲሁም መቀየር ከፈለጋችሁ "edit channel" የምትለዉን በተን ነክታችሁ
-የቻናሉን ስም
-ሎጎ
-የቻናል ባነር
-ዲስክሪፕሺ እና የመሳሰሉትን
መቀየር ትችላላችሁ።
በዚህ መልኩ የዩቲዩብ ቻናልን ከከፈታችሁ አበቃ ማለት አይደለም ገና ብዙ ማስተካከል ያለብን ነገር አለ። እና በዚሁ መተግበሪየ(አፕ) ላይ የዩቲዩብ ቻናል ከከፈታችሁ ቡኃላ ማሟላት ያለባችሁን ነገር በዉስጡ አካትቶ ስለያዘ የትም ሳትሄዱ በዚሁ መተግበሪያ(አፕ) ማግኘት ትችላላችሁ።
በዚህ ርዕስ የሚጠቅማችሁ ቪድዮዎች ከላይ 👍 አለላችሁ።
አስተያየት ይለጥፉ