ዩቲዩብ ለመጀመር ማሟላት ያለብን መሠረታዊ ነገሮች
አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለመጀመር የምንጀምርበት ነገር ሊያስፈልገን ይችላል። ልክ እንደዚያው ዩቲዩብን ለመጀመር የሚያስፈልገን ነገር አለ። ነገር ግን ዩቲዩብ ለመጀመር ያን ያህል የሚያስፈልገን ነገር የለም። ቢሆንም ግን ከታች ምን ምን ማሟላት እንዳለባችሁ ለአብነት ያህል ተቀምጦላቹሀል።
1, አንድሮይድ ወይም አይፖን ሞባይል
በቃ! ሌላ እንደጀማሪነት ምንም የሚያስፈልገን ነገር የለም። አሁን ለምሳሌ "SU TECK" የተሰኘዉን የዩቲዩብ ቻናል ብትመለከቱት የሚለቀቁ ቪድዮዎች
1, የሚቀረጹት
2, የሚቀነባበሩት
3, ቪድዮዎች የሚለቀቁት
4, ታምብኔሎችም የሚሰሩት
5, እና ሁሉም ነገር የሚከናወነዉ በሞባይል ብቻ ነዉ።
እናንተም ዩቲዩብን መጀመር ከፈለጋችሁ በእጃችሁ የያዛችሁት ቀፎ በቂ ነዉ።
ዩቲዩብ ጀምራችሁ ቻናላችሁ ካደገ (ገንዘብ መስራት ከጀመረ) በሂደት ልታሟሉ የምትችሉት ነገር ይኖራል።
ለምሳሌ:- ካሜራ
ትራይፖድ
gaming pc
ሪንግ ላይት እና ሌላኛዉንም
ነገር ልታሟሉ ትችላላችሁ።
ግን አሁን በያዛችሁት ቀፎ ዩቲዩብን ከመጀመር የሚያግዳችሁ ነገር አለ ብዬ አላስብም። አሁኑኑ በያዛችሁት ቀፎ የዩቲዩብ ቻናል መክፈት እና መጀመር ትችላላችሁ። የዩቲዩብ ቻናል እንዴት እደሚከፈት ማወቅ ከፈለጋችሁ እዚሁ መተግበሪያ(አፕ) ላይ አከፋፈቱን ማየት ትችላላችሁ።
አስተያየት ይለጥፉ