የዩቲዩብ ቻናል ሀሳቦች
የዩቲዩብ ቻናል ሀሳቦች
አንድ ዩቲዩበር ቻናል ከመክፈቱ አስቀድሞ ማሰብ ያለበት ቻናሉን ከከፈተ በኃላ ምን መስራት እንደሚችል(እንደሚፈልግ) ነዉ።
ብዙ ግዜ ሰዎች የዩቲዩብ ቻናል ከከፈቱ በኃላ በሁለት አይነት መንገድ ሲሰሩ ይስተዋላሉ
1.ፊታቸዉን እያሳዩ
ፊት ለፊት በካሜራ ተቀርጸዉ ቪድዮ የሚለቁት የቻናል አይነት ነዉ።
2.ፊታቸዉን ሳያሳዩ
ፊት ለፊት በካሜራ ሳይቀረጹ ድምጻቸውን ወይም ስክሪን ብቻ በመጠቀም የሚሰሩት የቻናል አይነት ነዉ።በዚህ ገጽ ከላይ በተጠቁሱት በሁለቱም የቻናል አይነቶች በርካታ የዩቲዩብ ቻናል ሀሳቦች አሉ ከታች ይዘረዘርላቹሀል።
ከታች የተዘረዘሩትን የቻናል ሀሳቦች ሶስት ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ መምረጥ አለባችሁ:
1.ለመስራት ቀላል የሆነ መሆን አለበት
የምትመርጡት የቻናል አይነት የማያለፋ እንዲሁም የትም ሆናችሁ መስራት የምትችሉት የቻናል አይነት መሆን አለበት። በተጨማሪም የምትመርጡት የቻል አይነት ቀላል እንዲሆንላችሁ ከተሰጥኦችሁ ጋር የሚቀራረብ የቻናል አይነት መሆን አለበት።2.ተመልካች በቀላሉ ማግኘት የሚችል መሆን አለበት
በመጀመሪያ ደረጃ ቀላል መሆኑን ስትመለከቱ ቀጥላችሁ ማየት ያለባችሁ ወሳኝ ነገር ተመልካች ያገኛል ወይስ አያገኝም የሚለዉን ነገር ነዉ። የዩቲዩብ ቻናል ከፍታችሁ ተመልካች ካላገኛችሁ ምንም ጥቅም የለዉም።3.ብዙም ቁስ የማይፈልግ መሆን አለበት
ይህ ማለት የምትመርጡት የቻናል አይነት ኮምፒውተር ባይኖራችሁ እንኳን በ አንድሮይድ ቀፎ መስራት የምትችሉት የቻናል አይነት መሆን አለበት ማለት ነዉ።ከላይ የተጠቁሱትን ሶስት ነገራቶች ታሳቢ አድርጋችሁ የቸናል አይነት መርጣችሁ ከጀመራችሁ በዩቲዩብ ስኬታማ የማትሆኑበት ምንም ምክኒያት የለም።
1.ፊታችሁን ሳታሳዩ መስራት የምትችሉት የቻናል አይነት:
1.1.የዜና ቻናል
የዜና ቻናል በኢትዮጵያ በርካታ ተመልካቾችን ማግኘት የሚችል እንዲሁም ለመስራት ቀላል የሆነ እና ፊታችንን ሳናሳይ አንደበታችንን ብቻ በመጠቀም መስራት የምንችለዉ የቻናል አይነት ነዉ። አንድ ዩቲዩበር የዜና ቻናል መስራት ከፈለገ
ማዘጋጀት የሚጠበቅበት ነገር
ታማኝ እና ፈጣን የመረጃ ምንጭ
በመቀጠልም ከቻለ ላፕቶፕ እና እና ከፍተኛ ጥራት ያለዉን ማይክ ማዘጋጀት አለበት።
ካልቻለ ደግሞ የአንድሮይድ ወይም አይፖን ቀፎ እና ትንሹን ማይክራፎን በመግዛት ካልሆነም ኢርፖን በመግዛት መጀመር ይችላል።
ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ቻናል የ አቤል ብርሀኑ የዜና ቻናል ነዉ
1.2.የሀይማኖታዊ ትምህርት ቻናል
ይህ የቻናል ስለ ሀይማኖታችን የምናስተምርበት እንዲሁም አንደበታችንን ብቻ በመጠቀም ፊታችንን ሳናሳይ መስራት የምንችልበት የቻናል አይነት ነዉ።
አንድ ዩቲዩበር የሀይማኖታዊ ቻናል መስራት ከፈለገ ማሟላት የሚጠበቅበት ነገር
➲በቂ እዉቀት
ከቻለ ኮምፒውተር እና ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ ያስፈልገዋል
ካልቻለ ደግሞ የአንድሮይድ ወይም የ አይፎን ቀፎ እና የማይክ ጥራት ያለዉ ኢርፖን ያስፈልገዋል።
ከላይ የተጠቀሰዉን ነገር አንድ ዩቲዩበር ማሟላት ከቻለ የሀይማኖት አስተምህሮት ቻናል መጀመር ይችላል።
1.3.የአፕልኬሽን ቻናል
ይህ የቻናል አይነት አዳዲስ እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑ የሞባይል አፕልኬሽኖችን ለሰዉ የምታስቃኙበት የቻናል አይነት ሲሆን አቀራረባችሁን የምታሳምሩ ከሆነ ተመልካች ማግኘት የምትችሉበት የቻናል አይነት ነዉ።
የአፕልኬሽን ቻናል ለመስራት ምን ያስፈልገናል?
➲የ አንድሮይድ ቀፎ እና ከተገኘ ማይክ ካልተገኘ ደግሞ በ አሪፍ ኳሊቲ ድምጻችንን ሊቀዳ የሚችል ኢርፎን ያስፈልገናል።
ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ቻናል የ እይታዬ ዩቲዩብ ቻናል ነዉ።
1.4.የቴክኖሎጂ ቻናል
ይህ የቻናል አይነት አለማችን ላይ የተገኙ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን የምታስቃኙበት የቻናል አይነት ነዉ።የቴክኖሎጂ ቻናል ለመስራት ምን ምን ያስፈልገናል?
ከተገኘ ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
1.5.የ አስገራሚ ክስተቶች ቻናል
ይህ የቻናል አይነት ደግሞ አለማችን ላይ የተከሰቱ አስገራሚ ነገሮችን የምናቀርብበት የቻናል አይነት ሲሆን በርካታ ተመልካቾችንም ማገኘት የሚችል የቻናል አይነት ነዉ።
የ አስገራሚ ክስተቶች ቻናል ለመስራት የሚያስፈልጉን ነገሮች
ከተቻለ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
1.6.የምርጥ አስር ወይም አምስት ቻናል
የቲዩብ መጀመር ያሰባቹ ሰዎች መቼም 'ኢትዮጵያ ላይ የሚገኙ 10 ከፍተኛ ተከፋይ ዩቲዩበሮች' የሚል ቪድዮ ብታገኙ መቼም ሳትመለከቱት ምታልፉት አይስለኝም ምክኒያቱም አንደኛዉ ተከፋይ ማን እንደሆነና ስንት እንደሚከፈለው ማወቅ ስለምትፈልጉ! የምርጥ አስር ወይም አምስት ቻናል ከፍተኛ ተመልካች ሊያገኙ ከሚችሉ የቻናል ዝርዝሮች ዉስጥ የሚመደብ የቻናል አይነት ነዉ። ይህን የቻናል አይነት ከመረጣችሁ በርካት ርዕሶችን ማግኘት ትችላላችሁ ይህ ማለት ደግሞ የቪድዮ ሀሳብ መቼም አይጠፋችሁም ማለት ነዉ።
የምርጥ አስር ወይም አምስት ቻናል ለመስራት የሚያስፈልጉን ነገሮች
ከተቻለ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
1.7.የምርቶች ግምገማ(review) ቻናል
ይህ የቻናል አይነት ደግሞ አዳዲስ ምርቶችን የምናስቃኝበት እንዲሁም ስለምርቱ ጥሩ እና መጥፎ ጎኑን የምናስረዳበት የቻናል አይነት ነዉ።የምርቶች ግምገማ(review) ቻናል ለመስራት የሚያስፈልጉን ነገሮች
ከተቻለ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
1.8.የጌም ቻናል
ይህ የቻናል አይነት ደግሞ ስለ አዳዲስ ጌሞች እንዲሁም ምርጥ ምርጥ የሆኑ ጌሞችን የምናመላክትበት የቻናል አይነት ነዉ።
የጌም ቻናል ለስራት የሚያስፈልገን
ከተቻለ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
2.ፊታችሁን እያሳያችሁ መስራት የምትችሉት የቻናል አይነት
2.1.የቭሎግ ቻናል
የቭሎግ ቻናል የራሳቹን የሂወት ተሞክሮ , አኗኗራችሁን, አዋዋላችሁን እና እና የመሳሰሉ ነገሮችን የምትሰሩበት አይነት ቻናል ሲሆን በርካታ ዩቲዩበሮች ይህን የቻናል አይነት እንደ ሁለተኛ ቻናል አድርገዉ ይጠቀሙታል ቲክቶከሮችም ዩቲዩብ ላይ ቻናል ከከፈቱ የቭሎግ ቻናል ነዉ የሚከፍቱት።የቭሎግ ቻናል ለመስራት ምን ምን ያስፈልገናል?
ከቻላችሁ
➲አሪፍ ጥራት ያለዉ ካሜራ ቢኖራችሁ ይመረጣል።
አልቻላችሁም
➲አሪፍ የካሜራ ጥራት ያለዉ ሞባይል ያስፈልጋቹሀል።
2.2.የ ሪያክሽን ቻናል
የ ሪያክሽን ቻናል አዝናኝ ቪድዮዎችን ከ ቲክቶክ, ፌስቡክ እና ከመሳሰሉ የሶሻል ሚድያዎች በማምጣት በቪድዮ ያላችሁን አመለካከት ለተመልካቾች በመግለፅ እንዲሁም ቪድዮን ለተመልካቾች በማሳየት የምትዝናኑበት እና የምታዝናኑበት የቻናል አይነት ነዉ። የ ሪያክሽን ቻናል በርካታ ተመልካቾችን እያገኙ ካሉ የቻናል አይነቶች ዉስጥ ይመደባል።የ ሪያክሽን ቻናል የሚያስፈልገን
ከተቻለ➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
➲ኮምፒውተር 🧑💻
አልተቻለ➲የአንድሮይድ ወይም የ አይፖን ሞባይል 📱
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
እንደምሳሌ የሚጠቀሰዉ ዩቲዩበር
Babi ነዉ።
2.3.የ ሾዉ ቻናል
የ ሾዉ ቻናል እንግዳ ወደ ቻናላችሁ በመጋበዝ ለሰዉ የምታስተዋውቁበት እንዲሁም ስመጥር የሆኑ ሰዎችን በመጋበዝ አዝናኝ ቆይታ የምታደርጉበት የቻናል አይነት ሲሆን ይህም የቻናል አይነት በርካታ ተመልካቾችን ማስገኘት የሚችል የቻናል አይነት ነዉ።
የ ሾዉ ቻናል ለመስራት ምን ምን ያስፈልገናል?
ይህን የቻናል አይነት ለመስራት በመጀመሪያ ቢያንስ በዩቲዩብ ታዋቂ መሆን አለባችሁ። በመቀጠልም
➲እራሳችሁን ከእንግዳችሁ ጋር ለተመልካቾች እየቀረጻችሁ የምታቀርቡበት ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ካሜራ 📷
➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
2.5.የ ጉብኝት(ትራቭል) ቻናል
ይህ የቻናል አይነት የተለያዩ አካባቢዎችን፣ ሀገሮችን፣ የመዝናኛ ማዕከሎችን እና የተለያዩ ባህሎችን የምታስጎበኙበት የቻናል አይነት ነዉ።የ ጉብኝት(ትራቭል) ቻናል ለስራት የሚያስፈልገን
➲እራሳችሁን እና የምታሰጎበኙትን ነገር ለተመልካቾች እየቀረጻችሁ የምታቀርቡበት ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ካሜራ 📷
➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
2.6.የቴክኖሎጂ ቻናል
2.7.የምርቶች ግምገማ(review) ቻናል
2.8.የጌሚንግ ቻናል
የጌሚንግ ቻናል ጌም እየተጫወታችሁ ተመልካቾቻችሁን የምታዝናኑበት የቻናል አይነት ነዉ። የጌሚንግ ቻናል አለማችን ላይ በዩቲዩብ ታዋቂ ከሚባሉ የቻናል አየነቶች አንዱ ነዉ።የጌሚንግ ቻናል ለመስራት ምን ያስፈልገናል?
➲ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለዉ ኮምፒውተር
➲እራሳችሁን ለተመልካቾች እየቀረጻችሁ የምታቀርቡት ካሜራ
➲አሪፍ ፍጥነት ያለዉ የ ኢንተርኔት አገልግሎት እና
➲ከፍተኛ ጥራት ያለዉ ማይክ 🎤
ከላይ የተጠቀሱትን ማሟላት ካልቻላችሁ የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቹሀል
➲ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለዉ ስማርት ቀፎ
➲እራሳችሁን ለተመልካቾች እየቀረጻችሁ የምታቀርቡት አሪፍ የካሜራ ጥራት ያለዉ ስማርት ቀፎ
➲አሪፍ ፍጥነት ያለዉ የ ኢንተርኔት አገልግሎት ሊኖራችሁ ይገባል
➲ድምጻችንን በጥሩ ሁኔታ የሚቀዳ ኤርፖን ያስፈልገናል።
ለተጨማሪ መረጃ 👇
Abrelo gamingን እና
Abyssinia gamerን መጠየቅ ትችላላችሁ።
1 አስተያየት